ዘላቂ ሰላምን ለማረጋገጥ በቁርጠኝነት መሥራት እንደሚገባ ተገለጸ።

47

ደብረታቦር: የካቲት 16/2017 ዓ.ም (አሚኮ) በፎገራ ወረዳ እና ወረታ ከተማ አሥተዳደር የሰላም አማራጮችን እና ኢኮኖሚያዊ ዕድገትን አጀንዳ ያደረገ የሕዝብ መድረክ ተካሂዷል።
በውይይቱ ላይ የደቡብ ጎንደር ዞን አሥተዳዳሪ ጥላሁን ደጀኔን ጨምሮ ሌሎች የዞን፣ የወረዳ የሥራ ኀላፊዎች፣ ከወረታ ከተማ እና ከፎገራ ወረዳ የተውጣጡ ተሳታፊዎች ተገኝተዋል።

የውይይቱ ተሳታፊዎች የአካባቢውን እና የክልሉን ሰላም በማረጋገጥ ኢኮኖሚው ላይ የተጠናከረ ሥራ መሥራት እንደሚያስፈልግ ተናግዋል። የሰላም እጦቱ ብዙ ዋጋ እያስከፈለን ነው ያሉት ተሳታፊዎቹ ሰላምን ለማስፈን የሃይማኖት አባቶች፣ የሀገር ሽማግሌዎች እና በየደረጃው የሚገኙ መሪዎች ቁርጠኛ ሊሆኑ ይገባል ብለዋል። ችግሮችንም በቅርበት እየተነጋገሩ መፍታት እንደሚያስፈልግ ጠቁመዋል።

የደቡብ ጎንደር ዞን አሥተዳደሪ ጥላሁን ደጀኔ ተገቢ ሀሳቦች እና አስተያየቶች በመድረኩ መነሳታቸውን ገልጸዋል። ከመሪ ድክመት ጋር በተያያዘ የተነሱ ጉዳዮችን ለማስተካከል እንሠራለን ብለዋል።
ለአካባቢም ኾነ ለክልል ሰላም ጠንቅ የኾኑ ችግሮችን በመፍታት ኢኮኖሚውን ማስተካከል እና ኢንቨስትመንትን ማበረታታት ይገባል ነው ያሉት።ዘላቂ ሰላምን ለማረጋገጥ እንደሚሠሩም ገልጸዋል።

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleየሰላም እና ደኅንነት ጉዳይ ትኩረት ሊሰጠው እንደሚገባ የደብረብርሃን ከተማ ሕዝባዊ ውይይት ተሳታፊዎች ተናገሩ።
Next articleየጦጢቶ ተንጠልጣይ የእግረኛ ድልድይ ተገንብቶ ለአገልግሎት ክፍት ኾነ።