የሰላም እና ደኅንነት ጉዳይ ትኩረት ሊሰጠው እንደሚገባ የደብረብርሃን ከተማ ሕዝባዊ ውይይት ተሳታፊዎች ተናገሩ።

33

ደብረ ብርሃን: 16/2017 ዓ.ም (አሚኮ) በደብረብርሃን ከተማ አሥተዳደር ሕዝባዊ ውይይት እየተካሄደ ነው።
የውይይቱ ተሳታፊዎች የሰላምና ደኅንነት ጉዳይ ትኩረት ሊሰጠው እንደሚገባ አንስተዋል። በሀገሪቱ የተለያዩ አካባቢዎች ያለው የሰላም እጦት ለከፍተኛ ችግር እየዳረገ በመኾኑ እልባት ሊሰጠው ይገባል ነው ያሉት።

በሰላም እጦቱ ምክንያት ከፍተኛ የኑሮ ውድነት እየተከሰተ ነው ያሉት ተሳታፊዎቹ ዜጎች ኑሯቸውን ለመምራት እየተቸገሩ ነው ብለዋል።
የዜጎች ነጻ እንቅስቃሴ እየተገደበ በመኾኑ ከተለያዩ አካባቢዎች ወደ ሌሎች አካባቢዎች የምርት እንቅስቃሴ እንዳይኖር አድርጓልም ብለዋል። ይህንን ለማስተካከል መንግሥት ሁነኛ መፍትሔ ሊያቀርብ ይገባል ነው ያሉት።

ብልጽግና ፓርቲ በሁለተኛው መደበኛ ጉባኤ ላይ ያስቀመጣቸው አቅጣጫዎችን ተግባራዊ ለማድረግም የሕዝቡን መሠረታዊ ችግሮች መፍታት ላይ ሊያተኩር ይገባል ብለዋል።
ሰላም የሁሉ ነገር መሠረት ነው ያሉት ተሳታፊዎቹ መንግሥት ሰላምን ማረጋገጥ እንደሚገባውም አንስተዋል።

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleየዓባይ ተፋሰስ አባል ሀገራት ሚኒስትሮች የታላቁ ሕዳሴ ግድብን ጎበኙ።
Next articleዘላቂ ሰላምን ለማረጋገጥ በቁርጠኝነት መሥራት እንደሚገባ ተገለጸ።