የዓባይ ተፋሰስ አባል ሀገራት ሚኒስትሮች የታላቁ ሕዳሴ ግድብን ጎበኙ።

61

ባሕር ዳር: የካቲት 16/2017 ዓ.ም (አሚኮ) የዓባይ ተፋስስ ሀገራት ሚኒስትሮች፣ ዲፕሎማቶች እና ጋዜጠኞች የታላቁ ኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብን ጎብኝተዋል።
በጉብኝቱ የኬንያ፣ ታንዛኒያ፣ ኡጋንዳ፣ ሱዳን፣ ደቡብ ሱዳንና የኢትዮጵያ የውኃ ሚኒስትሮችን ጨምሮ የተፋሰሱ ሀገራት ጋዜጠኞች ተሳትፈዋል።

የኢፌዴሪ ውኃና ኢነርጂ ሚኒስትር ኢንጅነር ሀብታሙ ኢተፋ ዶ.ር) እና የታላቁ ኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ዋና ሥራ አስኪያጅ ኢንጅነር ክፍሌ ሆሮ ለሚኒስትሮቹ ገለፃ አድርገዋል።
“የዓባይ ትብብርን ማጎልበት የአየር ንብረት ለውጥን ለመቋቋምና ለጋራ ብልፅግና” በሚል መሪ መልእክት 19ኛው የዓባይ (ናይል) ቀን በትናንትናው ዕለት መከበሩ ይታወቃል።

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous article“ብልጽግና ፓርቲ ሁሉንም አክብሮና አሳትፎ እውነተኛ መንገድ ይዞ እየተጓዘ ያለ ትልቅ ፓርቲ ነው” አቶ ይርጋ ሲሳይ
Next articleየሰላም እና ደኅንነት ጉዳይ ትኩረት ሊሰጠው እንደሚገባ የደብረብርሃን ከተማ ሕዝባዊ ውይይት ተሳታፊዎች ተናገሩ።