“ብልጽግና ፓርቲ ሁሉንም አክብሮና አሳትፎ እውነተኛ መንገድ ይዞ እየተጓዘ ያለ ትልቅ ፓርቲ ነው” አቶ ይርጋ ሲሳይ

28

ባሕር ዳር: የካቲት 16/2017 ዓ.ም (አሚኮ) በብልጽግና ፓርቲ ሁለተኛ መደበኛ ጉባዔ ላይ የተቀመጡ ውሳኔዎችና አቅጣጫዎች ላይ ያተኮረ የሕዝብ ኮንፍረንስ በሚዛን አማን ከተማ እየተካሄደ ነው። በኮንፈረንሱ መልዕክት ያስተላለፉት የብልጽግና ፓርቲ ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባል እና የአማራ ክልል ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት ኀላፊ ይርጋ ሲሳይ ብልጽግና ፓርቲ ኅብረ ብሔራዊነትን ባከበረ መልኩ ሀገረ መንግሥትን ለመገንባት የጀመረው ሂደት ውጤታማ መኾኑን ገልጸዋል።

“ብልጽግና ፓርቲ ሁሉንም አክብሮና አሳትፎ እውነተኛ መንገድ ይዞ እየተጓዘ ያለ ትልቅ ፓርቲ ነው ” ብለዋል። ሁሉም አንድ ኾነው ተባብረው ሠርተው የሚኖሩባት ጠንካራ ሀገረ መንግሥት ለመገንባት እየሠራ ያለ ፓርቲ መኾኑንም ተናግረዋል። ፓርቲው የሕዝብ ኃላፊነት ተሸክሞ ወደ ተግባር ከገባበት ጊዜ ጀምሮ ብዙ ተግዳሮቶች ቢገጥሙትም ፈተናዎችን ወደ መልካም ዕድል እየቀየረ በርካታ ስኬቶችን እያስመዘገበ መምጣቱን ገልጸዋል። በሁሉም ዘርፎች ወደ አገልግሎት የገቡና በግንባታ ሂደት ላይ የሚገኙ ትላልቅ ሀገራዊ ፕሮጀክቶች ለኢትዮጵያ ብልጽግና መስፈንጠሪያ መኾናቸውን አንስተዋል።

በፖለቲካ ዘርፍ አሰባሳቢ ትርክቶች መምጣቸውን የጠቀሱት አቶ ይርጋ ፓርቲው ቃሉን አክብሮ የሚፈጽም በመኾኑ በሁለተኛ መደበኛ ጉባዔው የተቀመጡ ውሳኔዎችንም በተግባር ያረጋግጣል ብለዋል። ፓርቲው ሕዝቡን እንደ ትልቅ አቅም ተጠቅሞ አሳታፊ በኾነ መልኩ የሚሠራ መኾኑንም አመልክተዋል።

ኢዜአ እንደዘገበው የቤንች ሸኮ ዞን ምክትል ዋና አሥተዳዳሪና የብልጽግና ፓርቲ ምክር ቤት አባል ሀብታሙ ካፍቲን በለውጡ መንግሥት በዞኑ አዎንታዊ ውጤቶች መመዝገባቸውን ተናግረዋል።
በዞኑ ግብርናን በማዘመን ምርትና ምርታማነት ማሳደግ እንደተቻለ ጠቅሰዋል። ዞኑ የተለያዩ ሀገራዊ ፕሮጀክቶች ባለቤት መኾኑን አመላክተዋል።

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleባለፉት ዓመታት የተከናወኑ ሁሉን አቀፍ ሥራዎች የሕዝብን ተጠቃሚነት ያሳደጉ መኾናቸውን የኢንዱስትሪ ሚኒስትሩ መላኩ አለበል ገለጹ።
Next articleየዓባይ ተፋሰስ አባል ሀገራት ሚኒስትሮች የታላቁ ሕዳሴ ግድብን ጎበኙ።