ባለፉት ዓመታት የተከናወኑ ሁሉን አቀፍ ሥራዎች የሕዝብን ተጠቃሚነት ያሳደጉ መኾናቸውን የኢንዱስትሪ ሚኒስትሩ መላኩ አለበል ገለጹ።

21

ባሕር ዳር: የካቲት 16/2017 ዓ.ም (አሚኮ) በሐረር ከተማ ሕዝባዊ ኮንፍረንስ እየተካሄደ ነው። በመድረኩ መልዕክት ያስተላለፉት የኢንዱስትሪ ሚኒስትሩ መላኩ አለበል ብልጽግና ፓርቲ ባለፉት ዓመታት ያከናወናቸው የልማት፣ የሰላም፣ የመልካም አሥተዳደርና ሌሎች ሥራዎች ሕዝቡን ተጠቃሚ ያደረጉ ናቸው ብለዋል።
ሕዝብ እና መንግሥትን በማስተባበር ሀገርን ማልማትና ማሻገር እንደሚቻል በግልጽ የታየበት መኾኑን አንስተዋል። በሐረሪ ክልልም የተከናወኑ የልማት ሥራዎች ነዋሪዎችን ተጠቃሚ ያደረጉና የሕዝቡን የልማት ጥያቄ የመለሱ ናቸው ብለዋል። መድረኩ ብልጽግና ፓርቲ ባለፉት ዓመታት ያከናወናቸውን እና በቀጣይ በሚያከናውናቸው ሥራዎች ላይ የሕዝብ ድጋፍና ትብብር ለማጎልበት የተዘጋጀ መኾኑን ተናግረዋል።

ከሐረሪ ክልል ኮሙዩኒኬሽን የተገኘው መረጃ እንደሚያመላክተው ያልተፈቱና ምላሽ ያላገኙ የልማት፣ የመልካም አሥተዳደር እና ሌሎች ሥራዎችን ለመፍታት ያለመ መኾኑንም አንስተዋል።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleሕዝባዊ የውይይት መድረክ በሚዛን አማን ከተማ እየተካሄደ ነው።
Next article“ብልጽግና ፓርቲ ሁሉንም አክብሮና አሳትፎ እውነተኛ መንገድ ይዞ እየተጓዘ ያለ ትልቅ ፓርቲ ነው” አቶ ይርጋ ሲሳይ