
ባሕር ዳር: የካቲት 16/2017 ዓ.ም (አሚኮ) በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል አሶሳ ከተማ ሕዝባዊ ኮንፈረንስ እየተካሄደ ነው።
ኮንፈረንሱ ብልጽግና ፓርቲ በሁለተኛ መደበኛ ጉባዔው ባሳለፋቸው ውሳኔዎችና አቅጣጫዎች ላይ ያተኮረ ነው።
በመድረኩ የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ሙፈሪያት ካሚል፣ በብልጽግና ፓርቲ የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ ኢሳቅ አብዱልቃድር እና ሌሎች የክልሉ ከፍተኛ የሥራ ኀላፊዎች ተገኝተዋል።
ኢዜአ እንደዘገበው ከክልሉ የተለያዩ አካባቢዎች የተውጣጡ የኅብረተሰቡ ክፍሎች በኮንፈረንሱ ላይ እየተሳተፉ ይገኛሉ።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!