በሐረር ከተማ ሕዝባዊ ውይይት እየተካሄደ ነው።

23

ባሕር ዳር: የካቲት 16/2017 ዓ.ም (አሚኮ) “ከቃል እስከ ባሕል” በሚል መሪ መልዕክት በሐረር ከተማ ሕዝባዊ ውይይት እየተካሄደ ነው ። ውይይቱ የብልጽግና ፓርቲ በሁለተኛ መደበኛ ጉባኤው ባሳለፋቸው ውሳኔዎች እና አቅጣጫዎች ላይ ያተኮረ ነው።

በመድረኩ የኢንዱስትሪ ሚኒስትር እና የብልጽግና ፓርቲ ሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባል መላኩ አለበል፣ በብልጽግና ፓርቲ የአፋር ክልል ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ እና የፓርቲው ሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባል መሐመድ ሁሴን እና ሌሎች ከፍተኛ ሥራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል።

በመድረኩ ለሚነሱ የሕዝብ ጥያቄዎች የብልጽግና ፓርቲ ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ እና የፓርቲው ምክር ቤት አባላት ምላሽና ማብራሪያ ይሰጣሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ ኤፍ ኤም ሲ ዘግቧል።

ከትላንት ጀምሮ በኢትዮጵያ ታላላቅ ከተሞች መካሄድ የጀመረው ሕዝባዊ ውይይት ዛሬም ቀጥሏል።

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleለሀገር የተከፈለ ዋጋ
Next articleአለመማር የት ያደርሰን ይኾን?