
በአጠቃላይ በኢትዮጵያ ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥርም 191 ደርሷል፡፡
ዛሬ እኩለ ቀን ላይ ጤና ሚኒስቴር ባወጣው መረጃ 25 ሰዎች በኮሮናቫይረስ እንደተያዙ አረጋግጦ ነበር። ሚኒስቴሩ አሁን ባወጣው መረጃ ደግሞ ተጨማሪ አራት ሰዎች ቫይረሱ እንደተገኘባቸው ገልጿል።
መደበኛ የ24 ሰዓት ዕለታዊ መግለጫ ከተሰጠ በኋላ በደረሰው አዲስ መረጃ መሠረት በትግራይ ክልል፣ በትግራይ ጤና ምርምር ኢንስቲትዩት በተደረገ 85 የላብራቶሪ ምርመራ ተጨማሪ አራት ሰዎች የኮሮና ቫይረስ እንደተገኘባቸው ነው ጤና ሚኒስቴር ያሳወቀው።
በዚህም መሠረት አዲስ ቫይረሱ የተገኘባቸው ሰዎች 29 ደርሰዋል። በአጠቃላይ በኢትዮጵያ ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥርም 191 ደርሷል፡፡
ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው አራቱም ኢትዮጵያዊያን ወንዶች ናቸው፤ አራቱም ታማሚዎች ከጅቡቲ የተመለሱና በመቀሌ አስገዳጅ ለይቶ ማቆያ የሚገኙ ናቸው ብሏል ሚኒስቴሩ።