“በሰላም እጦት ዋጋ ከፍለናል፣ ከዚህ በኋላ ዋጋ መክፈል የለብንም” ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ ጎሹ እንዳላማው

35

ባሕር ዳር: የካቲት 15/2017 ዓ.ም (አሚኮ) “ከቃል እስከ ባሕል” በሚል መሪ መልዕክት ሕዝባዊ ኮንፈረንስ በባሕር ዳር ከተማ ተካሂዷል።

ሕዝባዊ ኮንፈረንሱ የብልጽግና ፓርቲ በሁለተኛው መደበኛ ጉባኤ ባሳለፋቸው ውሳኔዎች እና ባስቀመጣቸው አቅጣጫዎች ላይ ያተኮረ ነው።

የባሕር ዳር ከተማ አሥተዳደር ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ ጎሹ እንዳላማው ሰላም የሁሉም ነገር መሠረት ነው፣ ሰላምን በአንድነት እና በኅብረት ማረጋገጥ አለብን ብለዋል። “በሰላም እጦት ዋጋ ከፍለናል፣ ከዚህ በኋላ ዋጋ መክፈል የለብንም” ነው ያሉት።

በሰላም እጦት ምክንያት ልጆቻችን ከትምህርት ገበታ ርቀዋል፣ ኢኮኖሚ ተጎድቷል፣ ንጹሐን ተጎድተዋል ብለዋል። ሰላምን በአንድነት እና በኅብረት መጠበቅ እንደሚገባም ተናግረዋል።

ለአማራ ሕዝብ የሚጠቅመው ሰላምን ማጽናት እና በኢኮኖሚ መጠናከር ነው ብለዋል። ከዚህ በኋላ የሰላም ችግር እንዳይኖር መንገዳችን ማስተካከል ይጠበቃል ነው ያሉት። ሰላምን ማረጋገጥ ከቻልን መጭው ዘመን የትንሣኤ እንጂ የሰቆቃ አይኾንም ብለዋል።

እስካሁን ድረስ የሄድንበት የመጠፋፋት አካሄድ አላዋጣንም ነው ያሉት። ቀጣዩ ጉዞ ፍቅር እና አንድነት የሞላበት ሊኾን እንደሚገባም ተናግረዋል።

የብልጽግና ፓርቲ ሁነኛ የኢትዮጵያን ችግር ለመፍታት የተቋቋመ መኾኑንም ተናግረዋል። ብልጽግና ፓርቲ ኢትዮጵያውያን በእኩልነት የሚጠቀሙበትን መድረክ የፈጠረ መኾኑን ገልጸዋል።

ብልጽግና ፓርቲ የአማራ ሕዝብ ጥያቄዎችን ለመመለስ በፕሮግራሙ አካቶ እየሠራ መኾኑንም ተናግረዋል።

ፓርቲው ኢትዮጵያዊነትን ለማጠናከር እየሠራ መኾኑንም አመላክተዋል። ወደፊት የሚኖረንን አካሄድ እና ጉዞ በማስተዋል ላይ የተመሠረተ መኾኑን አለበት ነው ያሉት። ሰከን ብሎ ማሰብ፣ አውድን መረዳት እና ትክክለኛውን ሀሳብ ማወቅ ይጠበቃል ብለዋል።

በመንግሥት መሥሪያ ቤት ውስጥ ኾኖ ሕዝብን የሚያማርር፣ ሕዝብ እና መንግሥትን የሚነጥል አለ ያሉት ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባው ከእናንተ ጋር ኾነን እናስተካክለዋለን ብለዋል። ታማኝ አገልጋዩን ከሀሰተኛው የመለየት ሥራ እንሠራለንም ነው ያሉት።

ከተማ አሥተዳደሩ የኑሮ ውድነትን ለማሻሻል እየሠራ መኾኑንም ገልጸዋል። ሕገወጥነትን እና ሌብነትን የመቆጣጠር ሥራ እየሠሩ መኾናቸውንም አንስተዋል።

ሕዝብን የሚያማርሩ አሠራሮችን እንደሚያስተካክሉም ገልጸዋል። ብልጽግና ፓርቲ ቃሉን በተግባር የሚፈጽም መኾኑንም አብራርተዋል።

ዘጋቢ፡-ታርቆ ክንዴ

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleከሁሉ አስቀድሞ ሰላምን ማረጋገጥ እንደሚገባ የባሕርዳር ሕዝባዊ ኮንፈረንስ ተሳታፊዎች ተናገሩ።
Next article15 ነጥብ 3 ቢሊዮን ብር የሚገመት የመንግሥት ሃብት ከብክነት ማዳኑን የአማራ ክልል ፍትሕ ቢሮ አስታወቀ።