
ደብረ ብርሃን: የካቲት 15/2017 ዓ.ም (አሚኮ) የደብረ ብርሃን ከተማ አሥተዳደር ዘመናዊ የገበያ ማዕከል ግንባታ መጀመሩን የንግድ እና ገበያ ልማት መምሪያው አስታውቋል።
በከተማው እቴጌ ጣይቱ ክፍለ ከተማ የሚገነባው የገበያ ማዕከል 8 ሺህ 129 ሄክታር ቦታ ላይ ያርፋል ተብሏል።
የደብረ ብርሃን ከተማ አሥተዳደር ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ በድሉ ውብሸት የገበያ ማዕከል ግንባታውን በአጭር ጊዜ ለማጠናቀቅ በትኩረት ይሠራል ብለዋል።
በሁሉም ክፍለ ከተሞች ማዕከላቱን በመገንባት “ምቹ የኾነ የግብይት ሥነ ሥርዓት ለመፍጠር በትኩረት እንደሚሠራ” ጠቁመዋል።
የደብረ ብርሃን ከተማ አሥተዳደር ንግድ እና ገበያ ልማት መምሪያ ኀላፊ ይርጋለም ምስጋናው አሁን ለተጀመረው የገበያ ማዕከል 196 ሚሊዮን ብር በጀት መያዙን ገልጸዋል።
የገበያ ማዕከል ግንባታውን በቦታው ተገኝተው የተመለከቱት የአማራ ክልል ንግድ እና ገበያ ልማት ቢሮ ኀላፊ ኢብራሂም ሙሀመድ (ዶ.ር) ከተማ አሥተዳደሩ ዋጋን በማረጋጋት እና ምቹ የገበያ ተቋማትን ለመገንባት በሚያደርገው ጥረት በቅርበት ክልሉ እንደሚደግፍ አረጋግጠዋል።
ዘጋቢ: ስንታየሁ ኃይሉ
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!