“ዘመን ኮንስትራክሽን ኮርፖሬሽን በሀገር ደረጃ ተመራጭ መኾን የቻለው በአፈጻጸም ሂደቱ ነው” ዋና አፈ ጉባኤ ፋንቱ ተስፋዬ

38

ባሕር ዳር: የካቲት 15/2017 ዓ.ም (አሚኮ) የዘመን ኮንስትራክሽን ኮርፖሬሽን አዲስ የስም እና የንግድ ምልክት ይፋ አድርጓል።

በዚህ መርሐ ግብር ላይ ተገኝተው መልዕክት ያስተላለፉት የአማራ ክልል ምክር ቤት ዋና አፈ ጉባኤ ፋንቱ ተስፋዬ ድርጅቱ የኮርፖሬሽን ደረጃ እስኪደርስ በኮንስትራክሽን ዘርፉ የራሱን ድርሻ እየተወጣ እንደነበር ተናግረዋል።

ዋና አፈ ጉባኤዋ ዘመን ኮንስትራክሽን ኮርፖሬሽን የተቋቋመበት ዋና ዓላማ የመንግሥትን የገበያ ክፍተት ለመሙላት ታሳቢ ተደርጎ ስለመኾኑ አስገንዝበዋል።

ኮርፖሬሽኑ አሁን ላይ ከክልሉም ተሻግሮ ሀገራዊ ሥራዎችን እየሠራ ያለ ሲኾን ወደ ፊትም በዓለም አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪ ለመኾን ታሳቢ አድርጎ እየሠራ ስለመኾኑ ገልጸዋል።

ዋና አፈ ጉባኤ ፋንቱ ኮርፖሬሽኑ ከዚህ ለመድረስ በርካታ ችግሮችን እና ውጣውረዶችን እንዳሳለፈም ነው ያብራሩት።

ኮርፖሬሽኑ የሚገጥሙትን ሳንካዎች በጥበብ እያለፈ በሀገር ደረጃ ተመራጭ መኾን የቻለ መኾኑን ገልጸው ለዚህም የአፈጻጸም ሂደቱ ተመራጭ እንዲኾን እንዳደረገው ጠቁመዋል።

ዋና አፈ ጉባኤዋ ዘመን ኮንስትራክሽን ኮርፖሬሽን ከዚህ በፊት የገጠመውን እና አሁን ያለውን ሁኔታ እያሰላሰለ እና እየመረመረ በመሥራቱ ውጤት አምጥቷል ሲሉ አስረድተዋል።

ዘመን ኮንስትራክሽን ኮርፖሬሽን ለውጥ እና ውጤት እንዲያመጣ የመሪዎች፣ የሠራተኛው እና የቦርዱ ጥረት በቀላሉ እንደማይታይ ነው ያስገነዘቡት።

በሀገር ደረጃ በኮንስትራክሽን ደረጃ የራሱን የማይተካ ሚና ለመወጣት ኮርፖሬሽኑ ብዙ መድከሙን አስረድተዋል። በተለይ በገጠር የሠራቸው ሥራዎች አርዓያ መኾን የሚችሉ ስለመኾናቸውም ገልጸዋል።

ለአንድ ድርጅት ስኬት የሰው ኀይሉ ወሳኝ ነው ያሉት ዋና አፈ ጉባኤ ፋንቱ አሁን የተገኘውን ውጤት በማላቅ እና ችግሮችን በጥበብ በመፍታት በኮንስትራክሽን ዘርፉ የበለጠ አሻራቸውን እንዲያስቀምጥ አደራ ብለዋል።

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleጾመ ኢየሱስን በፈጣሪ የተከለከሉ ግብረ ኃጥያትን ባለመፈጸም መጾም እንደሚገባ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ አሳሰቡ።
Next articleለማዕከላዊ ጎንደር ዞን ለሦስት ወረዳዎች እና ለሦስት የጤና ተቋማት የተሽከርካሪ ድጋፍ ተደረገ።