ጾመ ኢየሱስን በፈጣሪ የተከለከሉ ግብረ ኃጥያትን ባለመፈጸም መጾም እንደሚገባ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ አሳሰቡ።

19

አዲስ አበባ: የካቲት 15/2017 ዓ.ም (አሚኮ) የኢትዮጵያ ኦርቶዶክ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ፓትርያሪክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ የ2017 ዐቢይ ጾምን አስመልክቶ የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል።

የጾመ ኢየሱስ ሱባኤ ዋና ዓላማ ዲያቢሎስን ድል መንሳት መኾኑን የገለጹት ብጹዕነታቸው ኢየሱስ ክርስቶስ አርባ የቀን እና አርባ ለሊት ሲጾም በዲያቢሎስ መፈተኑን አንስተዋል። በእርግጥም በአጽዋማት ወቅት ፈተናዎች ይበዛሉ ያሉት ፓትርያሪኩ ከጌታችን ጾም የምንወስደው ትምህርት የዲያቢሎስን ፈተና በመንፈስ ልዕልና ማለፍ እንደሚቻል ነው ብለዋል።

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ምዕመናንም አስተምህሮውን መነሻ በማድረግ ታላቁን የዐቢይ ጾም በፈጣሪ የተከለከሉ ግብረ ኃጥያትን ባለመፈጸም በመልካም የመንፈስ ልዕልና መጾም እንደሚገባ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ገልጸዋል።

ወርሃ ጾሙን ሰብዓዊ ክብር እንዳይነካ በመጸለይ፣ ከነገሮች ሁሉ ለሰላም እና እኩልነት ቅድሚያ በመስጠት፣ የተቸገሩትን በመርዳት በአጠቃላይ በመልካም ሥራ ማሳለፍ እንደሚገባም ብፁዕነታቸው መልእክት አስተላልፈዋል።

ዘጋቢ: ቤተልሄም ሰለሞን

የአሚኮየአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን

Previous article“አንድነት፣ ኅብረት እና ፍቅር ለሁላችን ይበጀናል” ቢቂላ ሁሪሳ (ዶ.ር)
Next article“ዘመን ኮንስትራክሽን ኮርፖሬሽን በሀገር ደረጃ ተመራጭ መኾን የቻለው በአፈጻጸም ሂደቱ ነው” ዋና አፈ ጉባኤ ፋንቱ ተስፋዬ