ሕዝባዊ ኮንፈረንስ በአዲስ አበባ ከተማ ቦሌ ክፍለ ከተማ ተጀመረ።

29

አዲስ አበባ: የካቲት 15/2017 ዓ.ም (አሚኮ) በሀገር አቀፍ ደረጃ እየተካሄደ የሚገኘው ሕዝባዊ ውይይት በአዲስ አበባ ከተማ ቦሌ ክፍለ ከተማ ተጀምሯል::

ብልጽግና ፓርቲ በሁለተኛ መደበኛ ጉባኤው ባስቀመጣቸው አቅጣጫዎች ላይ ትኩረቱን አድርጎ በ25 ከተሞች እየተካሄደ ባለው ሕዝባዊ ውይይት የአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪዎችም በቦሌ ክፍለ ከተማ ተገኝተው ውይይት እያደረጉ ይገኛሉ::

በአዲስ አበባ ቦሌ ክፍለ ከተማ እየተካሄደ ያለውን ሕዝባዊ ውይይትም ሞገስ ባልቻ የአዲስ አበባ ከተማ አሥተዳደር ብልጽግና ፓርቲ ኀላፊ፤ ዓለሚቱ ኡሞድ የብልጽግና ፓርቲ ማዕከላዊ ኮሚቴ አባል እና የጋምቤላ ክልል ፕሬዝዳንት፤ እንደሻው ጣሰው (ዶ.ር) የብልጽግና ፓርቲ ማዕከላዊ ኮሚቴ አባል እና የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ፕሬዝዳንት እየመሩት ይገኛሉ::

በሕዝባዊ ውይይቱ ላይ የአዲስ አበባ ከተማ አሥተዳደር እና የፌደራል መንግሥት ከፍተኛ የሥራ ኀላፊዎችም ተገኝተዋል::

አሚኮም በቦታው ተገኝቶ መረጃዎችን እየተከታተለ ያደርሳል::

ዘጋቢ: ሰለሞን አሰፌ

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous article“የደሴ ሕዝብ በትምህርት በኩል ሞዴል መኾኑን አስመስክሯል” የደሴ ከተማ አሥተዳደር
Next article“የሰላም ተምሳሌት የኾነች ባሕር ዳርን ስላሳያችሁን እናመሰግናችኋለን” ርእሰ መሥተዳደር ጥላሁን ከበደ