
አዲስ አበባ: የካቲት 15/2017 ዓ.ም (አሚኮ) ብልጽግና ፓርቲ ባካሄደው ሁለተኛ መደበኛ ጉባኤው ያሳለፋቸው ውሳኔዎች እና ያስቀመጣቸው አቅጣጫዎችን በሚመለከት በኦሮሚያ ክልል አዳማ ከተማ ሕዝባዊ ውይይት እያካሄደ ነው።
በውይይቱ የገቢዎች ሚኒስቴር ሚኒስትር አይናለም ንጉሴ፣ የሲዳማ ክልል ርእሰ መሥተዳደር ደስታ ሌዳሞ፣ የክልሉ ከፍተኛ የሥራ ኀላፊዎች፣ አባ ገዳዎች፣ ሀደስንቄዎች እና ሌሎች የኅብረተሰብ ክፍሎች ተገኝተዋል።
ሀገር አቀፍ ሕዝባዊ ውይይቱ ከዛሬ ጀምሮ በ25 ዋና ዋና ከተሞች እንደሚካሄድ እና ኮንፈረንሱ በብልጽግና ፓርቲ ሥራ አሥፈጻሚ ኮሚቴ እንደሚመራ ከፓርቲው የተገኘው መረጃ ያመላክታል።
ዘጋቢ፦ ቴዎድሮስ ደሴ
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!