የደሴ ከተማ እግር ኳስ ክለብን ለመደገፍ ያለመ ሕዝባዊ ሩጫ እየተካሄደ ነው።

47

ደሴ: የካቲት 15/2017 ዓ.ም (አሚኮ) በኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ እየተሳተፈ የሚገኘውን የደሴ ከተማ እግር ኳስ ክለብን በገንዘብ ለመደገፍ ዓላማ ያደረገ “እኔም ለደሴ” በሚል መሪ መልዕክት ሕዝባዊ ሩጫ እየተካሄደ ነው።

በከፍተኛ ሊጉ ምድብ “ለ” የሚገኘው ደሴ ከተማ የመጀመሪያውን ዙር በቀዳሚነት ያጠናቀቀ ሲኾን አሁንም ምድቡን በ24 ነጥብ እየመራ ነው።

የደጋፊ ማኅበሩ ሠብሣቢ ሀብታሙ ጌታቸው “ክለቡ ወደ ፕሪሚየርሊግ ለማደግ የሚያደርገውን ጉዞ በገንዘብ ለመደገፍ እና አጋርነታችንን ለማሳየት የሩጫ ውድድሩ ተዘጋጅቷል” ብለዋል።

የደሴ ከተማ ወጣቶች እና ስፖርት መምሪያ ኀላፊ ሰይድ አራጋው የደሴ ከተማ እግርኳስ ክለብ በቀጣይ ዓመት የፕሪሚየርሊግ ተሳታፊ እንዲኾን እየተሠራ ይገኛል ነው ያሉት።

ለዚህ ይረዳ ዘንድ ከተማ አሥተዳደሩ ክለቡን በገንዘብ ከመደገፍ ባለፈ ደጋፊ ማኅበሩን በገቢ ለማጠናከር እንደሚሠራ አመላክተዋል።

በከፍተኛ ሊጉ እየተሳተፈ ጥሩ ውጤት በማስመዝገብ ላይ የሚገኘውን የደሴ ከተማ እግርኳስ ክለብ በገንዘብ ለማጠናከር ዓላማ ባደረገው የሩጫ ውድድር ከሕጻናት እስከ አዋቂ በርካታ የደሴ እና አካባቢዋ ነዋሪዎች እየተሳተፉበት ነው።

ዘጋቢ :-ተመስገን አሰፋ

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleየመድኃኒት አስመጭዎች እና አምራቾች በመድኃኒት አቅርቦት ላይ ያሉ ችግሮችን ሊፈቱ ይገባል።
Next articleሕዝባዊ ውይይት በአዳማ ከተማ እየተካሄደ ነው።