ከፍተኛ የሥራ ኀላፊዎች ሕዝባዊ ኮንፈረንስ ለማካሄድ ባሕር ዳር ከተማ ገቡ።

70

ባሕር ዳር: የካቲት 14/2017 ዓ.ም (አሚኮ) ከፍተኛ የሥራ ኀላፊዎች ሕዝባዊ ኮንፈረንስ ለማካሄድ ባሕር ዳር ከተማ ገብተዋል። ባሕር ዳር የገቡት የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ርእሰ መሥተዳድር ጥላሁን ከበደ፣ የብልጽግና ፓርቲ የሕዝብ እና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ዘርፍ ኀላፊ ቢቂላ ሁሪሳ (ዶ.ር) ናቸው።

ከፍተኛ የሥራ ኀላፊዎቹ ባሕር ዳር ሲገቡ የአማራ ክልል ርእሰ መሥተዳድር አረጋ ከበደ፣ የባሕር ዳር ከተማ አሥተዳደር ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ ጎሹ እንዳላማው፣ የአማራ ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት የአደረጃጀት ዘርፍ ኀላፊ ፍስሃ ደሳለኝን ጨምሮ ሌሎች ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኀላፊዎች አቀባበል አድርገውላቸዋል።

ከፍተኛ የሥራ ኀላፊዎቹ ነገ በባሕር ዳር ከተማ የሚካሄደውን ሕዝባዊ ኮንፈረንስ እንደሚመሩ ይጠበቃል። በባሕር ዳር ከተማ በሚኖራቸው ቆይታ የልማት ሥራዎችንም ይጎበኛሉ ተብሏል።

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous article“በሦስተኛ ዙር የተማሪዎች ምዝገባ ንቅናቄ ከ5 ሺህ በላይ ተማሪዎችን መመለስ ተችሏል” የምዕራብ ጎጃም ዞን
Next articleየመድኃኒት አስመጭዎች እና አምራቾች በመድኃኒት አቅርቦት ላይ ያሉ ችግሮችን ሊፈቱ ይገባል።