
ጎንደር: የካቲት 14/2017 ዓ.ም (አሚኮ) በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የመንግሥት ተጠሪ ተስፋዬ በልጅጌ (ዶ.ር) እና የገንዘብ ሚኒስትር ድኤታ እዮብ ተካልኝ (ዶ.ር) ጎንደር ከተማ ገብተዋል።
የከፍተኛ የሥራ ኀላፊዎች ጎንደር ከተማ ሲደርሱ የጎንደር ከተማ አሥተዳደር ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ ቻላቸው ዳኘው፣ የማዕከላዊ ጎንደር ዞን አሥተዳዳሪ አወቀ አስፈሬ፣ የከተማ አሥተዳደሩ ከፍተኛ አመራሮች፣ የሃይማኖት አባቶች፣ የሀገር ሽማግሌዎች፣ ታዋቂ ግለሰቦች በተገኙበት በአፄ ቴዎድሮስ የአየር ማረፊያ አቀባበል ተደርጎላቸዋል።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን