
ባሕር ዳር፡ ሚያዝያ 29/2012 ዓ.ም (አብመድ) በኢትዮጵያ፣ ፓኪስታን፣ ህንድ እና ማዕከላዊ አፍሪካ ሰኔ 14 ቀን 2012 ዓ.ም ቀለበታዊ የፀሐይ ግርዶሽ እንደሚከሰት የኢትዮጵያ ስፔስ ሳይንስ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት አስታወቀ፡፡
በኢትዮጵያ የፀሐይ ግርዶሹ ከምዕራብ እስከ ሰሜን ምሥራቅ የሀገሪቱ ክፍል በተለይም በላልይበላ አካባቢ ከጠዋቱ 12፡45 እስከ ቀኑ 6፡33 እንደሚቆይ የኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር ሰሎሞን በላይ (ዶክተር) ገልፀዋል፡፡
እንደ ኢብኮ ዘገባ በዕለቱም ከረፋዱ 3፡40 አካባቢ ለተወሰኑ ሴኮንዶች ጨለማ እንደሚፈጠርም ዋና ዳይሬክተሩ ጠቁመዋል፡፡