
ደብረ ብርሃን: የካቲት 14/2017 ዓ.ም (አሚኮ) በደብረ ብርሃን ከተማ አሥተዳደር እና በሰሜን ሸዋ ዞን ያለውን ሰላማዊ እንቅስቃሴ ለማጽናት ያለመ ምክክር በደብረ ብርሃን ከተማ እየተካሄደ ነው። በውይይቱ ላይ በምክትል ርእሰ መሥተዳድር ማዕረግ የከተማ ዘርፍ አስተባባሪ እና የአማራ ክልል የከተማ እና መሠረተ ልማት ቢሮ ኀላፊ አሕመዲን መሐመድ (ዶ.ር) አካባቢው በጸጥታ ሥራው ራሱን በመቻል ምዕራፍ ላይ የሚገኝ መኾኑን ተናግረዋል።
“ወረዳዎች እና ከተሞች ዘላቂ ሰላማቸውን እንዲያሰፍኑም እየተሠራ እየተሠራ ነው” ብለዋል። ክልሉ ቀደም ሲል ባከናወናቸው ተግባራት የጸጥታ መዋቅሩን በማጠናከር ሰላም የማስፈን ሥራ በሰፊው ሠርቷል ነው ያሉት።
በሀገር መከላከያ ሠራዊት የኮማንዶ እና አየር ወለድ እዝ አዛዥ እና የማዕከላዊ ሸዋ የሰላም ካውንስል ሰብሳቢ ሌተናል ጀኔራል ሹማ አብደታ በጸጥታ አካላት ጠንካራ ቅንጅታዊ አሠራር እየተተገበረ መኾኑን ገልጸዋል።
በውይይቱ የመከላከያ መኮንኖች፣ የዞን፣ የከተማ አሥተዳደር እና የወረዳ መሪዎች ተገኝተዋል።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!