የማኅበረሰብ አቀፍ ጤና መድኅን አገልግሎትን ለማሳደግ እየሠራ መኾኑን የአዊ ብሔረሰብ አሥተዳደር ጤና መምሪያ አስታወቀ።

31

እንጅባራ: የካቲት 14/2017 ዓ.ም (አሚኮ) መምሪያው የ2017 በጀት አመት 2ኛ ዙር የማኅበረሰብ አቀፍ ጤና መድኅን አገልግሎት አፈጻጸም ባለድርሻ አካላት በተገኙበት በእንጅባራ ከተማ እየገመገመ ነው።

የአዊ ብሔረሰብ አሥተዳደር ጤና መምሪያ ኀላፊ አየለ አልማው የኅብረተሰቡን ፍትሐዊ የጤና አገልግሎት ተደራሽነት ለማረጋገጥ ማኅበረሰብ አቀፍ ጤና መድኅን አገልግሎትን ሽፋን ማሳደግ ሁነኛ መፍትሔ መኾኑን ተናግረዋል። የማኅበረሰብ አቀፍ የጤና መድኅን አገልግሎትን ለማሳደግ እየሠሩ መኾናቸውን ገልጸዋል።

በበጀት ዓመቱ ከ261 ሺህ በላይ አባዎራዎች የአገልግሎቱ ተጠቃሚ ለማድረግ ታቅዶ ባለፉት ወራት በተከናወኑ ሥራዎች የዕቅዱን 53 በመቶ ማሳካት ተችሏልም ነው ያሉት። ከዚህ ውስጥ ከ73 ሺህ በላይ የሚኾኑት መክፈል በማይችሉት ማዕቀፍ መንግሥት ወጪያቸውን የሚሸፍንላቸው እንደኾነም ገልጸዋል።
በጎ ፈቃደኛ ግለሰቦች እና ድርጅቶች በማስተባበር የ891 አባዎራዎች ዓመታዊ የጤና መድኅን ወጪ እንዲሸፈንላቸው መደረጉንም አንስተዋል።

በተፈጠረው የጸጥታ ችግር ምክንያት 119 ቀበሌዎች አሁንም የአገልግሎቱ ተጠቃሚ አለመኾናቸውን ያነሱት ኀላፊው በእነዚህ አካባቢዎች ሊደርስ የሚችለውን የጤና ቀውስ ለመቀነስ የሁሉንም ድጋፍ ይጠይቃል ብለዋል።

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን

Previous articleኢትዮጵያ ከፍተኛ የደኅንነት እና ጥራት ደረጃዎችን አሟልቶ የተሠራ አዲስ የኤሌክትሮኒክስ ፓስፖርት ይፋ አደረገች።
Next article“ወረዳዎች እና ከተሞች ዘላቂ ሰላማቸውን እንዲያሰፍኑ እየተሠራ ነው” አሕመዲን መሐመድ (ዶ.ር)