
ባሕር ዳር: የካቲት 13/2017 ዓ.ም (አሚኮ) ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኀላፊዎች የመገጭ ግድብ ፕሮጄክትን ጎብኝተዋል። በጉብኝቱ የሰላም ሚኒስትር መሐመድ እድሪሰ፣ የጠቅላይ ሚኒስትሩ የማኅበራዊ ጉዳይ አማካሪ ሙዓዘጥበባት ዲያቆን ዳንኤል ክብረት፣ የብሔራዊ ባንክ ገዥ ማሞ እስመለዓለም ምህረቱ፣ የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንት ዓለምአንተ አግደው እና የጎንደር ከተማ አሥተዳደር ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ ቻላቸው ዳኘው ተገኝተዋል።
በጉብኝታቸውም ፕሮጄክቱ በተያዘለት ጊዜ እየተከናወነ መኾኑን መመልከታቸውን ገልጸዋል። የመገጭ ግድብ በልዩ ትኩረት እና ክትትል እየተሠራ የሚገኝ ፕሮጀክት ነው። ፕሮጄክቱ ሲጠናቀቅ የጎንደር ከተማ አሥተዳደርን የንጹሕ መጠጥ ውኃ ችግር እንደሚቀርፍ ይጠበቃል። ግድቡ ከንጹሕ መጠጥ ውኃ ባሻገር ለመስኖ ልማት አገልግሎት ይሰጣል።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!