
ባሕር ዳር: የካቲት 13/2017 ዓ.ም (አሚኮ) የአማራ ክልል ኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን የነባር እና የአዲስ ፕሮጀክቶች የአፈፃፀም ግምገማ እና በቀጣይ ሥራዎች ዙሪያ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር ውይይት አድርጓል። የአማራ ክልል ኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ዋና ሥራ አሥፈጻሚ ብርሃኑ ጣምአለው ከግብርና ወደ ኢንዱስትሪ የሚደረገውን ሽግግር የሚያግዙ ዓለም አቀፍ ደረጃቸውን የጠበቁ የተቀናጁ አግሮ ኢንዱስትሪ ፓርኮች እና የገጠር የሽግግር ማዕከላት ግንባታ እየተከናወነ መኾኑንም ገልጸዋል። ኮርፖሬሽኑ 88 ነባር እና በአዲስ ፕሮጀክቶችን እያስገነባ መኾኑን አንስተዋል።
ከሚገነቡት ፕሮጄክቶች ዘመናዊውን የፍሳሽ ማጣሪያ እና አያያዝ ልማት፣ የመካከለኛ ኀይል ማስተላለፊያ መሥመር፣ የፓርኩን ደረጃ የሚያሻሽሉ ሲሲቲቪ ካሜራ እና የዳታ ማዕከላት፣ የግብይት ማዕከል፣ የምርት መቀበያ እና ማቀነባበሪያ ማዕከል፣ የንጹሕ መጠጥ ውኃ መሠረተ ልማት ግንባታ፣ የአርሶ አደሮች ሕንጻዎች እና የአንድ ማዕከላት አገልግሎት ይገኙበታል።
ፕሮጀክቶቹ ከ3 ቢሊዮን ብር በላይ በጀት ተመድቦላቸዋል ነው ነው ያሉት። የፕሮጀክቶቹን ግንባታ በፍጥነት በማጠናቀቅ ወደ ተሟላ ሥራ ለማስገባት ትኩረት ተደርጓል ብለዋል። የነበሩ መልካሞ ተሞክሮዎችን ይበልጥ በማጠናከር፣ የነበሩ ችግሮችን ደግሞ በመፍታት በቀጣይ ወራት የተጀመሩ ፕሮጀክቶችን መፈጸም እንደሚገባም ነው ያስገነዘቡት።
ዘጋቢ፦ ዳግማዊ ተሠራ
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!