
ደብረ ብርሃን: የካቲት 13/2017 ዓ.ም (አሚኮ) በደብረ ብርሃን ጤና ሳይንስ ኮሌጅ የተከታታይ ሙያ ማጎልበቻ ማዕከል ተመርቆ ለአገልግሎት ክፍት ኾኗል። የተከታታይ ሙያ ማጎልበቻ ማዕከል ተመርቆ ለአገልግሎት ክፍት መኾኑ በጤናው ዘርፍ እየሠሩ ያሉ ባለሙያዎችን ክህሎት በማሳደግ ረገድ ጉልህ ሚና ይኖረዋል ተብሏል።
በጤና ሳይንስ ኮሌጁ ውስጥ የተቋቋመው ይህ ማዕከል በዩኒሴፍ ድጋፍ መከናወኑ ተገልጿል። የደብረ ብርሃን ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ዲን ማሙዬ አይተንፍሱ ማዕከሉ የባለሙያዎችን ክህሎት በማሳደግ የጤና አገልግሎቱ ላይ የራሱን አወንታዊ ሚና እንዲጫወት ያስችላል ብለዋል።
በሥነ ሥርዓቱ የደብረ ብርሃን ከተማ አሥተዳደር ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ በድሉ ውብሸት፣ የአማራ ክልል ጤና ቢሮ የሥራ ኀላፊዎች፣ የዩኒሴፍ ተወካይ እና በድርጅቱ የእናቶች፣ ጨቅላ ሕፃናት፣ የልጆች እና የወጣቶች ጤና ኀላፊ ቲየሴ ቺሙና እና ሌሎች የሥራ ኀላፊዎች ተገኝተዋል።
ዘጋቢ፦ በላይ ተስፋዬ
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!