154

ሰዎች ያለሐኪም ትዕዛዝ የሚወስዷቸው መድኃኒቶች የኮሮና ቫይረስ ስርጭትን በቀላሉ የመለየት ሥራ ላይ እንቅፋት እንደሚሆኑ ተገለጸ፡፡

ባሕር ዳር፡ ሚያዝያ 29/2012 ዓ.ም (አብመድ) ሰዎች በተለያዩ አጋጣሚዎች የሚገጥሟቸውን የጤና ቀውሶች ጊዜያዊ ወይም ዘላቂ መፍትሔ ለማግኘት በሕክምና ባለሙያዎች የሚታዘዙ መድኃኒቶችን ይጠቀማሉ፡፡ አንዳንዶች ግን ከሕክምና ባለሙያዎች ትዕዛዝ ውጭ ሕመማቸውን ለማስታገስ በራሳቸው ፈቃድ መድኃኒቶችን ይወስዳሉ። ይህ ደግሞ የጎንዮሽ ጉዳቱ ከፍ ያለ ነው።

‘‘የሰዎች የመድኃኒት ፍላጎትና አወሳሰድ ግንዛቤ ከኮሮና ወረርሽ መምጣት በኋላ ምን ደረጃ ላይ ነው? የትኞቹ መድኃኒቶችስ በብዛት የኮሮና ቫይረስ ከመጣ ወዲህ ፍላጎታቸው ጨመረ?’’ የሚሉ ጥያቄዎችን ይዘን ባለሙያዎችን አነጋግረናል፤ የፋርማሲ ባለሙያው ኤልያ አወል ደግሞ ትዝብታውን ለአብመድ አጋርተዋል፡፡ ‘‘ክሎሮኪን፤ አድቪን እና ሌሎች የራስ ምታት ማስታገሻዎችን የሚገዙ ሰዎች ቁጥር በየለቱ እየጨመረ ነው’’ ብለዋል፡፡

ሰዎች በኮሮና ዙሪያ ያላቸው ግንዛቤ አናሳ መሆኑን ያነሱት ባለሙያው ከወረርሽኙ በኋላ የራስ ምታት እና የሰውነት ሙቀት መጨመር ሲገጥማቸው ባልተለመደ መልኩ እየወሰዷቸው ያሉ የማስታገሻ መድኃኒቶች ቁጥሩ ከፍ ማለቱን አመላክተዋል፡፡

ዶክተር ወልደሰንበት ዋጋነው የድንገተኛና ጽኑ ሕክምና ስቴሻሊስት እና የኮሮና ቫይረስ ሕክምና አማካሪና የቡድን አስተባባሪ ናቸው፡፡ ከወቅቱ የኮሮና ቫይረስ መስፋፋት ጋር በተያያዘ ዜጎች ማንኛውም ሕመምም ሆነ የሕመም ስሜት የገጠመው ሰው የሚወስዳቸው መድኃኒቶች የቫይረሱን ስርጭት በቀላሉ የመለየት ሥራ ላይ እንቅፋት እንደሚሆኑ አንስተዋል፡፡

ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ ደግሞ ዓለም የገጣማትን የኮሮና ወረርሽኝ ተከትሎ ከዚህ ቀደም ለማስታገሻነትም ሆነ ሕመሞችን ለመፈወስ በሚል የሚወሰዱ ዘመናዊና የባህል መድኃኒቶች ከመቸውም ጊዜ በላይ ጥንቃቄ ሊወሰድባቸው እና የሕክምና ባለሙያን ትዕዛዝ የተከተሉ ሊሆን እንደመሚገባ ዶክተር ወልደሰንበት አሳበዋል።

ዘጋቢ፡- ጋሻው ፈንታሁን -ከአዲስ አበባ

Previous articleፍርሃትና ግዴለሽነት ዋጋ እንዳያስከፍሉ መጠንቀቅና የእርምት ርምጃ እንዲወሰድ ባለሙያዎች አሳሰቡ፡፡
Next articleከሦስት ዓመት በፊት የተከሰተው እና በየጊዜው ብቅ እያለ በሰብል ላይ ጉዳት የሚያደርሰውን ሁሉን አውዳሚ ተምች በመደበኛ ተባይነት ፈርጆ እየሠራ መሆኑን የአማራ ክልል ግብርና ቢሮ አስታወቀ፡፡