ከፍተኛ መሪዎች በባቲ ከተማ የልማት ፕሮጀክቶችን እየጎበኙ ነው።

13

ከሚሴ: የካቲት 13/2017 ዓ.ም (አሚኮ) የክልል እና የዞን ከፍተኛ መሪዎች በአማራ ክልል ኦሮሞ ብሔረሰብ አሥተዳደር በባቲ ከተማ እየተገነቡ ያሉ የትምህርት ተቋማትን፣ የሥራ ዕድል ፈጠራ እና ሌሎች የልማት ሥራዎችን እየጎበኙ ነው።

በጉብኝቱ የአማራ ክልል ምክር ቤት አፈጉባኤ ፋንቱ ተስፋዬ፣ የአማራ ክልል ምክትል ርእሰ መሥተዳድር አብዱ ሁሴን (ዶ.ር) እና የአማራ ክልል ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት የአደረጃጀት ዘርፍ ኀላፊ ፍሰሃ ደሳለኝን ጨምሮ ሌሎች ከፍተኛ የሥራ ኀላፊዎች ተገኝተዋል።

የትምህርት ተቋማት ግንባታ እና የሥራ ዕድል ፈጠራ ፕሮጀክቶች የከተማዋን ዕድገት ለማፋጠን እና የሕዝቡን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ የሚያስችሉ ናቸው ተብሏል። የመሪዎቹ ጉብኝት የልማት ፕሮጀክቶችን ለማበረታታት እና የሕዝቡን ተሳትፎ ለማሳደግ ያለመ ነው ተብሏል።

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!

https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous article“የተጀመሩ ሥራዎችን መጨረስ፣ አጀንዳዎችን መቅረጽ እና ይፋ ማድረግ የቀጣይ አቅጣጫዎች ናቸው” ፕሮፌሰር መስፍን አርዓያ
Next article“ቴክኖሎጂን መጠቀም ግልጽነት እና ተጠያቂነት ያለው አሥተዳደር እንዲኖር ያስችላል” ጋሻው አወቀ (ዶ.ር)