“የተጀመሩ ሥራዎችን መጨረስ፣ አጀንዳዎችን መቅረጽ እና ይፋ ማድረግ የቀጣይ አቅጣጫዎች ናቸው” ፕሮፌሰር መስፍን አርዓያ

42

አዲስ አበባ: የካቲት 13/2017 ዓ.ም (አሚኮ) የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ባለፉት ሦስት ዓመታት ያከናወናቸውን ዐበይት ሥራዎች እና የቀጣይ የትኩረት አቅጣጫዎች አስመልክቶ ለሚዲያ ባለሙያዎች ገለጻ አድርጓል። በኮሚሽኑ የተከናወኑ ተግባራትን አስመልክተው ማብራሪያ የሰጡት የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ዋና ኮሚሽነር ፕሮፌሰር መስፍን አርዓያ በ11 ክልሎች እና በሁለቱ ከተማ አሥተዳድሮች የምክክር ተሳታፊዎችን የመለየት ሥራ ተሠርቷል ብለዋል። የተሳታፊዎች ልየታን ለማጠናቀቅ 92 በመቶ መድረሱን ዋና ኮሚሽነሩ ገልጸዋል።

ኮሚሽኑ ሥራው ዘግይቶ በነበረበት በአማራ ክልል በጎንደር፣ ባሕር ዳር፣ ደሴ እና ስሜን ሽዋ የተሳታፊ ልየታ እና የተባባሪዎች ሥልጠና መጠናቀቁን አንስተዋል። ኢትዮጵያ አሁን ላለችበት ሁኔታ መሠረታዊ የኾኑ መንስኤዎችን ለመለየት ብዙ መንገድ ተሂዶ አዲስ ምዕራፍ መከፈቱን አንስተዋል፡፡ ኮሚሽነሩ የፖለቲካ አለመረጋጋት፣ ግጭት፣ የተዛቡ መረጃዎች ስርጭት፣ የፖለቲካ ፓርቲዎች ሁሉም ወደ ምክክሩ አለመምጣት እና በትጥቅ ትግል ላይ ያሉ ወገኖች አጀንዳቸውን ይዘው አለመቅረባቸው ፈተና ኾኖ መቆየቱንም ጠቁመዋል።

ኮሚሽኑ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የተሰጠውን የአንድ ዓመት ተጨማሪ የሥራ ዘመን ተጠቅሞ በአማራ እና በትግራይ ክልሎች የተጀመሩ ሥራዎችን መጨረስ፣ አጀንዳዎችን መቅረጽ እና ይፋ ማድረግ፣ የምክክር ጉባኤ አመካካሪ እና አመቻቾችን መለየት፣ ማሠልጠን እና ምክክር ማድረግ የቀጣይ የትኩረት አቅጣጫ ናቸው ብለዋል።

ዘጋቢ፡- ቤተልሄም ሰለሞን

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!

https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleየሚሊሻ አባላት ለሕዝብ በመታመን ለዘላቂ ሰላም መረጋገጥ እንዲተጉ የደብረ ማርቆስ ከተማ አሥተዳደር አሳሰበ።
Next articleከፍተኛ መሪዎች በባቲ ከተማ የልማት ፕሮጀክቶችን እየጎበኙ ነው።