በደብረ ብርሃን ከተማ የሚገኙ ጤና ተቋማት ለተገልጋዮች ምቹ እንዲኾኑ የተሠራው ሥራ ለሌሎች አካባቢዎች በምሳሌነት የሚነሳ ነው።

21

ደብረ ብርሃን: የካቲት 13/2017 ዓ.ም (አሚኮ) በደብረ ብርሃን ከተማ አሥተዳደር ጤና መምሪያ ስር የተሠሩ የጤና ልማት ሥራዎች የክልል እና የዞን የጤና የሥራ ኀላፊዎች እና ባለሙያዎች የሚሳተፉበት የልምድ ልውውጥ እየተካሄደ ነው። የጤና ተቋማትን ጽዱ፣ ማራኪ እንዲኾኑ እና የአገልግሎት አሰጣጣቸው እንዲዘምን ማድረግ ይገባል ተብሏል።

የአማራ ክልል ጤና ቢሮ ምክትል ኀላፊ ገስጥ ጥላሁን በደብረ ብርሃን ከተማ ያለው የጤና መሠረተ ልማት እና የተቋማት አሥተዳደር ለሌሎች አካባቢዎችም በአርዓያነት የሚነሳ መኾኑን ተናግረዋል። በከተማዋ እየተሠሩ ያሉ የተቋማት ማስፋፊያ ሥራዎች እና የተቋማት ምቹነት ጉብኝት እየተካሄደ ነው።

ዘጋቢ፦ በላይ ተስፋዬ

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleታጥቀው በጫካ የነበሩ ታጣቂዎች የሰላም አማራጭን ተቀበሉ።
Next articleየሚሊሻ አባላት ለሕዝብ በመታመን ለዘላቂ ሰላም መረጋገጥ እንዲተጉ የደብረ ማርቆስ ከተማ አሥተዳደር አሳሰበ።