
ባሕር ዳር: የካቲት 13/2017 ዓ.ም (አሚኮ) ነፍጥ አንግበው በአማራ ክልል በጎጃም ቀጣና ሲንቀሳቀሱ የነበሩ ታጣቂዎች የሰላምን አማራጭን ተቀብለዋል። የታጣቂ ቡድን አባላቱ ከዓመት በላይ የትጥቅ ትግል ላይ የቆዩ መኾናቸውን ጠቅሰዋል። ሁኔታው የሕዝብን ጥያቄ ማስመለስ የሚል ሽፋን ቢኖረውም ውስጡ ግን የግል ጥቅም ማሳደድ እንደኾነ ተናግረዋል።
አሁን ላይ የሄዱበት መንገድ የተሳሳተ መኾኑን በመረዳታቸው ወደ ሰላማዊ አማራጮችን መቀበላቸውን ነው የገለጹት።
ጫካ በቆዩባቸው ጊዜያት በሕዝባቸው ላይ በደል መፈጸማቸውን የጠቀሱት የታጣቂ ቡድኑ አባላት በቀጣይ ራሳቸውን ወደ ሰላማዊ ሕይወት በማስገባት የበደሉትን ሕዝብ ለመካስ ዝግጁ መኾናቸውን ተናግረዋል።
መንግሥት ባቀረበው የሰላም አማራጭ አማካኝነት በርካታ ታጣቂዎች የሰላም አማራጭን እየተቀበሉ ነው።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!