
እንጅባራ: የካቲት 13/2017 ዓ.ም (አሚኮ) በምረቃ ሥነ ሥርዓቱ የአዊ ብሔረሰብ አሥተዳደር ዋና አሥተዳዳሪ ቴዎድሮስ እንዳለው እና የአዊ ብሔረሰብ ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ሙሉዓዳም እጅጉን ጨምሮ ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ታድመዋል።
የአዊ ልማት ማኅበር ሥራ አሥኪያጅ ጌታዬ ሁነኛው ሁለገብ የገቢ ማስገኛ ሕንጻው በሁለት ዓመት ጊዜ ውስጥ ተገንብቶ የተጠናቀቀ ሲኾን ከ94 ነጥብ 5 ሚሊዮን ብር በላይ ወጭ ተደርጎበታል ብለዋል።
ሕንጻው ለቢሮ፣ ለመኝታ፣ ለመሠብሠቢያ አዳራሽ፣ ለካፌ እና ለሌሎችም አገልግሎቶች የሚውሉ የተለያዩ ክፍሎችን የያዘ እንደኾነም ተናግረዋል።
የሕንጻው መገንባት ልማት ማኅበሩ የመንግሥት የልማት ክፍተቶችን ለመሸፈን ለሚያደርገው ጥረት ተጨማሪ የኢኮኖሚ አቅም የሚፈጥር እንደኾነም ሥራ አሥኪያጁ ገልጸዋል።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!