የአማራ ገጠር መንገዶች ኮንስትራክሽን ኤጀንሲ የተቀናጀ የሀብት አጠቃቀም ሶፍትዌር የምረቃ ሥነ ሥርዓት እየተካሄደ ነው።

51

ባሕር ዳር: የካቲት 13/2017 ዓ.ም (አሚኮ) በአማራ ገጠር መንገዶች ኮንስትራክሽን ኤጀንሲ የተቀናጀ የሀብት አጠቃቀም ሶፍትዌር የምረቃ ሥነ ሥርዓት እየተካሄደ ነው የሚገኘው። የተቋሙ 30ኛ ዓመት የምሥረታ በዓልም የሥነ ሥርዓቱ አካል ነው። በማስጀመሪያ ሥነ ሥርዓቱ የአማራ ክልል ርእሰ መሥተዳድር አረጋ ከበደን ጨምሮ ሌሎች የክልሉ ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኀላፊዎች ተገኝተዋል።

የለማው ሶፍትዌር ሥራን ቀላል፣ ቀልጣፋ እና የተቀናጀ አድርጎ ለመምራት እንደሚያስችል ተመላክቷል። ሶፍትዌሩ የሰው ኀይልን፣ የንብረት አሥተዳደርን እና ለሌሎች በቴክኖሎጂ ለማሥተዳደር እና ለመቆጣጠር የሚያስችል መኾኑ ተመላክቷል።

በታርቆ ክንዴ

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous article“የእርሻ ውል ሥርዓት ምርት እና ምርታማነትን በማሳደግ ረገድ ድርሻው ከፍተኛ ነው” አቶ አጀበ ስንሻው
Next articleየአዊ ልማት ማኅበር በእንጅባራ ከተማ ያስገነባውን ባለ ስድስት ፎቅ ሁለገብ የገቢ ማስገኛ ሕንጻ አስመረቀ።