
ባሕር ዳር: የካቲት 13/2017 ዓ.ም (አሚኮ) የአምራች ኢንዱስትሪ ዘርፉን ማስፋፋት ለምናልመው ብልፅግና ወሳኝ ነው ሲሉ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ ገለጹ።
ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ የአማራ ብረታ ብረት ኢንዱስትሪና ማሽን ቴክኖሎጂ ልማት ኢንተርፕራይዝ ለብልፅግና የሚኖረውን አበርክቶ ጠቁመዋል።
በዚህም በባሕር ዳር ከተማ በኢንተርፕራይዙ የተመረቱት ስማርት ፖሎች፣ የዲች ከቨሮች እና ሌሎች ምርቶች በክልሉ እየተሠሩ ላሉ የኮሪደር ልማቶች ጥቅም ላይ መዋል መጀመራቸውን ነው በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት የገለጹት።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን