
ባሕር ዳር: የካቲት 12/2017 ዓ.ም (አሚኮ) የአማራ ክልል ገቢዎች ቢሮ የ2017 በጀት ዓመት የሰባት ወራት ዕቅድ አፈፃፀምን ገምግሟል። የአማራ ክልል ገቢዎች ቢሮ በ2017 በበጀት ዓመት ከመደበኛ እና ከከተማ አገልግሎት 71 ነጥብ 65 ቢሊዮን ብር ለመሠብሠብ አቅዶ በሰባት ወሩ ከ31 ቢሊዮን 86 ሚሊዮን ብር በላይ መሠብሠቡን አስታውቋል።
ሰሜን ሸዋ፣ ዋግኽምራ ብሔረሰብ አሥተዳደር እና ደቡብ ወሎ ዞኖች የተሻለ ገቢ መሠብሰባቸው ተመላክቷል። የግብር ከፋዮችን ማኅደር አያያዝ ማዘመን፣ የደረጃ ሽግግር፣ የቀን ገቢ ግምት ጥናት፣ የውዝፍ ገቢ መረጃ ማጥራት፣ የከተማ አገልግሎት እና የሊዝ ገቢ በቀጣይ ትኩረት የሚሰጣቸው ጉዳዮች መኾናቸውን የቢሮው ምክትል ኀላፊ ፍቅረማርያም ደጀኔ ገልጸዋል።
ከደረጃ “ሐ” ግብር ከፋዮች መሠብሠብ ያለበት ገቢ እየተሠበሠበ እንዳልኾነ ተነስቷል። ከገቢዎች ቢሮ የተገኘው መረጃ እንደሚያመላክተው የክልሉን ልማት ለማፋጠን በቀጣይ ተጨማሪ ጥናት ማካሄድ እና ተመጣጣኝ ገቢ መሠብሠብ ይገባል ተብሏል።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!