
ወልድያ: 12/2017 ዓ.ም (አሚኮ) የክልል እና የዞን ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኀላፊዎች በወልድያ ከተማ አሥተዳደር እየተሠሩ ያሉ የልማት ሥራዎችን እየጎበኙ ነው።
በጉብኝቱ የአማራ ክልል ምክር ቤት አፈጉባኤ ፋንቱ ተስፋዬ፣ የአማራ ክልል ምክትል ርእሰ መሥተዳድር አብዱ ሁሴን (ዶ.ር) ጨምሮ የክልል እና የዞን ከፍተኛ የሥራ ኀላፊዎች ተገኝተዋል።
ከፍተኛ የሥራ ኀላፊዎቹ የ30 ሜትር ስፋት ያለው የውስጥ ለውስጥ ቀለበት መንገድ ጎብኝተዋል። መንገዱ በ750 ሚሊዮን ብር በከተማ አሥተዳደሩ ሙሉ ወጭ የሚሠራ መኾኑ ተመላክቷል።
በከተማ አስተዳደሩ እየተገነቡ ያሉ የገበያ ማዕከል እና ዲጂታል የሕዝብ ቤተመጻሕፍት ተጎብኝተዋል። ቤተ መጻሕፍቱ በ16 ነጥብ 5 ሚሊየን ብር በከተማ አሥተዳደሩ ሙሉ ወጭ የሚገነባ ነው። የገበያ ማዕከሉ በከተማ አሥተዳደሩና በክልል መንግሥት በጀት እየተሠራ መኾኑ ተገልጿል።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን