ስደት ዓለም አቀፍ ችግር በመኾኑ ዓለም አቀፍ ትብብርን ይጠይቃል።

29

አዲስ አበባ: የካቲት 12/2017 ዓ.ም (አሚኮ) የካርቱም ፕሮሰስ አካል የኾነ የስደተኞች እና የስደት ተመላሾችን ጉዳይ የሚመክር መድረክ በአዲስ አበባ ከተማ እየተካሄደ ነው፡፡ የአውሮፓ ኅብረት የአፍሪካ ቀንድ የፍልሰት መስመር ተነሳሽነት በመባል የሚታወቀዉ የካርቱም ፕሮሰስ በአፍሪካ ቀንድ እና በአውሮፓ መካከል ያሉ የስደት ፈተናዎችን ለመፍታት እ.ኤ.አ. በ2014 በጣሊያን ሮም በተካሄደው የሚኒስትሮች ኮንፈረንስ የተመሠረተ ነዉ፡፡

በመድረኩ መልዕክት ያስተላለፉት የዉጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ምስጋኑ አርጋ ስደትን እና ከስደት ጋር ተያይዞ የሚያጋጥሙ ችግሮችን ለማለፍ የካርቱም ፕሮሰስ መድረክ ተጠናክሮ መቀጠል አለበት ብለዋል፡፡ የአውሮፓ ኅብረት ኮሚሽን ተወካይ ሚስተር ሮበርት ሪቢክ ስደቶኞችን እና ከስደት ተመላሾችን በአግባቡ ለማሥተዳደር እና ተግባሩ ውጤታማ ይሆን ዘንድ የአውሮፓ ኅብረት ኮሚሽን ድጋፉን አጠናክሮ እንደሚቀጥል ተናግረዋል፡፡

የካርቱም ፕሮሰስ ሊቀመንበር ዋኤል ባዳዊ (ዶ.ር) ለአሚኮ እንደተናገሩት “ስደት ዓለም አቀፍ ችግር በመኾኑ ዓለም አቀፍ ትብብርን ይጠይል” ብለዋል። የካርቱም ፕሮሰስን ለመመሥረት መነሻዉም አስቸጋሪነቱ እንደኾነ ነው የገለጹት። ስደተኞችን በተገቢዉ መንገድ መመለስ እና የተመለሱትን መልሶ ማቋቋም ቁልፍ አጀንዳ ማድረግ እንደሚያስፈልግም ተገልጿል።

ዘጋቢ: በለጠ ታረቀኝ

የአሚኮየአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን

Previous articleየውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጌዲዮን ጢሞቴዎስ (ዶ.ር) ከኖርዌይ አቻቸው ጋር ተወያዩ።
Next article“ከተሞች ያላቸውን ትስስር አጠናክው በጋራ እንዲያድጉ አስፈላጊው ድጋፍ እና ክትትል ይደረጋል” አቶ ፋንታ ደጀን