
ባሕር ዳር: የካቲት 12/2017 ዓ.ም (አሚኮ) የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጌዲዮን ጢሞቴዎስ (ዶ.ር) ከኖርዌይ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ኤስፒን ባርት አይድ ጋር ተወያይተዋል።
የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ከኖርዌይ አቻቸው ጋር በአፍሪካ ቀንድ ሰላም እና ጸጥታ ዙሪያ መክረዋል። ሚኒስትሮቹ በሁለቱ ሀገራት መካከል የአየር ንብረት ለውጥን ለመከላከል እና በአረንጓዴ ኢኮኖሚ ልማት ዙሪያ ተባብሮ መሥራት በሚችሉባቸው ጉዳዮች ዙሪያ መምከራቸውን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የተገኘው መረጃ ያመላክታል።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!