ሩሲያ በዓለም አቀፍ መድረኮች የኢትዮጵያን ጥቅም ለማስከበር ከኢትዮጵያ ጎን እንደምትቆም አፈጉባኤ ታገሠ ጫፎ ገለጹ።

26

ባሕር ዳር: የካቲት 12/2017 ዓ.ም (አሚኮ) የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ታገሠ ጫፎ የሩሲያ ፌዴሬሽን ምክር ቤት ሊቀመንበር ሚስዝ ቫለቲና ማትቬንኮ የተመራ የልዑካን ቡድንን በጽሕፈት ቤታቸው ተቀብለው አነጋገረዋል፡፡ አፈጉባዐለው ሩሲያ ከኢትዮጵያ ጋር ረጅም ጊዜ ወዳጅነት እንዳላት ገልጸዋል። ወዳጅነቱ በምጣኔ ሃብታዊ ትብብር ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ተናግረዋል።

ሩሲያ በዓለም አቀፍ መድረኮች የኢትዮጵያን ጥቅም ለማስከበር ከኢትዮጵያ ጎን እንደምትቆም ያነሱት አፈ ጉባኤው ግንኙነቱ ወደፊትም ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ነው ገለጹት፡፡ የሁለቱን ሀገራት ግንኙነት የበለጠ ለማጠናከር በፓርላሜንታዊ ፣ በንግድ፣ በኢንቨስትመንት እና የንግዱን ማኅበረሰብ ያሳተፉ ሥራዎች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉም አመላክተዋል።

ከሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የተገኘው መረጃ እንደሚያመላክተው ኢትዮጵያ እና ሩሲያ የብሪክስ አባል ሀገራት በመኾናቸው በብሪክስ መድረክ ትብብራቸውን አጠናክሮ ለማስቀጠል እንደሚሠራም ገልጸዋል። የሩሲያ ፌዴሬሽን ምክር ቤት ሊቀመንበር ሚስዝ ቫለቲና ማትቬንኮ የሁለቱን ሀገራት የቆየ የወዳጅነት ግንኙነት በምጣኔ ሃብት፣ በንግድ እና ኢንቨስትመንት ለማስቀጠል ሀገራቸው ፍላጎት እንዳላት ተናግረዋል፡፡

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!

https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleየአዲስ አበባ ከተማ አሥተዳደር ከ1 መቶ 11 ቢሊዮን ብር በላይ ገቢ መሠብሠቡን ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገለጹ።
Next articleየውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጌዲዮን ጢሞቴዎስ (ዶ.ር) ከኖርዌይ አቻቸው ጋር ተወያዩ።