
ባሕር ዳር: የካቲት 12/2017 ዓ.ም (አሚኮ) የካቲት 12 ለሀገራችን ያለንን ፍቅር እና ዘመን ተሻጋሪ የኾነ ጽናታችንን የምናሳይት ነው ሲሉ ፕሬዝዳንት ታዬ አጽቀሥላሴ ተናገሩ፡፡
ፕሬዝዳንቱ በማኅበራዊ ትሥሥር ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት የካቲት 12 የመስዋዕታችንን ፋይዳ የምናስብበት ዕለት ነው ብለዋል፡፡
የካቲት 12 የሰማዕታት ቀን የኢትዮጵያውያን የፀረ-ቅኝ ግዛት ተጋድሎ፣ ለነፃነት ያለን ቀናዒነት፣ ለሀገራችን ያለንን ፍቅር፣ ዘመን ተሻጋሪ የኾነውን ጽናታችን እና የመስዋዕታችንን ፋይዳ የምናስብበት ዕለት ነውም ብለዋል።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!