
ወልድያ: የካቲት 12/2017 ዓ.ም (አሚኮ) የክልል እና የዞን ከፍተኛ የሥራ ኀላፊዎች ከራያ ቆቦ እና ከቆቦ ከተማ አሥተዳደር ነዋሪዎች ጋር እየተወያዩ ነው።
ውይይቱን የአማራ ክልል ምክር ቤት አፈጉባኤ ፋንቱ ተስፋዬ፣ የአማራ ክልል ምክትል ርእሰ መሥተዳድር አብዱ ሁሴን (ዶ.ር)፣ የአማራ ክልል የብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት የአደረጃጀት ዘርፍ ኀላፊ ፍስሃ ደሳለኝ እና የሰሜን ወሎ ዞን አሥተዳደሪ አራጌ ይመር እየመሩት ነው።
በውይይቱ የክልል እና የዞን ከፍተኛ የሥራ ኀላፊዎች ተገኝተዋል። ውይይቱ በሰላም፣ በልማትና መልካም አሥተዳደር ጉዳዮች ዙሪያ ላይ ያተኮረ ነው።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!