88ኛው የሰማዕታት መታሰቢያ በአዲስ አበባ አየተከበረ ነው።

48

ባሕር ዳር: የካቲት 12/2017 ዓ.ም (አሚኮ) 88ኛው የየካቲት 12 የሰማዕታት መታሰቢያ በዓል በአዲስ አበባ ስድስት ኪሎ የሰማዕታት ሐውልት እየተከበረ ይገኛል።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ባሕል፣ ኪነ ጥበብ እና ቱሪዝም ቢሮ ኀላፊ ሂሩት ካሳው (ዶ.ር) የጥንታዊት ኢትዮጵያ ጀግኖች የአርበኞች ማኅበር ፕሬዝዳንት ልጅ ዳንኤል ጆቴ የአበባ ጉንጉን አስቀምጠዋል።

በበዓሉ ላይ የሃይማኖት አባቶች፣ የአርበኞች ልጆች እና ሌሎች የመንግሥት የሥራ ኀላፊዎች መገኘታቸውን ኢፕድ ዘግቧል።

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

Previous articleያለውን የመልማት እድል በአግባቡ ለመጠቀም ሰላም ያስፈልጋል።
Next articleለሀገር የተከፈለ ሰማዕትነት!