ያለውን የመልማት እድል በአግባቡ ለመጠቀም ሰላም ያስፈልጋል።

26

ደብረ ብርሃን: የካቲት 11/2017 ዓ.ም (አሚኮ) በምክትል ርእሰ መሥተዳደር ማዕረግ የከተማ ልማት ዘርፍ አሥተባባሪ እና የአማራ ክልል ከተማና መሰረተ ልማት ቢሮ ኀላፊ አሕመዲን መሐመድን (ዶ.ር) ጨምሮ ሌሎች የክልሉ እና የሰሜን ሸዋ ዞን የመንግሥት ከፍተኛ የሥራ ኀላፊዎች በወረዳው ያለውን የኢንቨስትመንት እንቅስቃሴ ተዘዋውረው ተመልክተዋል።

ዶክተር አሕመዲን ወረዳው ከፍተኛ የመልማት አቅም ስላለው እና ማኅበረሰቡም አምራች በመኾኑ ያንን ምርት በግብአትነት የሚጠቀም ኢንዱስትሪ ያስፈልጋል ብለዋል። እስካሁንም በከተማው የተገነቡት አምራች ፋብሪካዎች ተኪ ምርት በማምረት እና የውጭ ምንዛሬ በማስቀረት ትልቅ አቅም ፈጥረዋል ብለዋል። የአረርቲ ሴራሚክ ፋብሪካን በአብነትም አንስተዋል።

የልማት ጉዞውን የሚመጥን እና ፍላጎትን መሰረት ያደረገ የመኖሪያ ቤት ችግርን የሚፈታ ሪል እስቴት ግንባታም መኖሩን አበረታተዋል። በተለይም የአገልግሎት እና አምራች ዘርፉ የበለጠ እንዲለማ ማኅበረሰቡ ለሰላም በጋራ መሥራት ይገባል ብለዋል። የሰሜን ሸዋ ዞን ዋና አሥተዳዳሪ መካሻ አለማየሁ ወረዳው ገና ያልተነካ የብዙ ሀብት ባለቤት በመኾኑ ወደ ልማት ቀይሮ ተጠቃሚ መኾን ያስፈልጋል ብለዋል። ይህ እንዲሳካ ግን ማኅበረሰቡ የሰላም ባለቤት መኾን እንዳለበት አሳስበዋል፡፡

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን

Previous article14 ሚሊዮን ማሳ በሁለተኛ ደረጃ ካዳስተር በመመዝገብ ዲጂታላይዝድ መደረጉን መሬት ቢሮ አስታወቀ።
Next article88ኛው የሰማዕታት መታሰቢያ በአዲስ አበባ አየተከበረ ነው።