
ባሕር ዳር: የካቲት 11/2017 ዓ.ም (አሚኮ) የምስራቅ ዕዝ ዋና አዛዥ ሌተናል ጄኔራል መሐመድ ተሰማ፣ የዕዙ ኮማንድ፣ የኮር አዛዦች፣ የክፍለ ጦር አመራሮች እና ከፍተኛ መኮንኖች የባሕር ዳር ስታዲዮምን፣ የዓባይ ድልድይን እና መናፈሻዎችን ጎብኝተዋል።
በክልሉ እየተከናወኑ ያሉ የመሠረተ ልማት ሥራዎች ዕዙ እየከፈለ ባለው መስዋዕትነት እና ባመጣው ሰላም የተገኙ ውጤቶች መኾናቸውን የጉብኝቱ ተሳታፊዎች ተናግረዋል።
ቀጣይም ዘላቂ ሰላምን በማጽናት ሌሎች ሰፋፊ ፕሮጀክቶች እንዲሠሩ ማድረግ እንደሚገባም ከኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ድረ ገጽ የተገኘው መረጃ ያመለክታል።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!