በጎንደር ከተማ የተከናወኑ የልማት ሥራዎች የከተማዋን ታሪካዊነት የሚመጥኑ መኾናቸውን የአሚኮ ጎንደር ቅርንጫፍ ሠራተኞች ተናገሩ።

47

ጎንደር: የካቲት 11/2017 ዓ.ም (አሚኮ) የአማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን ጎንደር ቅርንጫፍ ሠራተኞች በጎንደር ከተማ አሥተዳደር እየተሠሩ ያሉ የልማት ሥራዎችን ጎብኝተዋል።

ሠራተኞቹ በከተማዋ የተሠራውን የኮሪደር ልማት እና የአፄ ፋሲለደስ ቤተ መንግሥት እድሳትን ተመልክተዋል። በምልከታቸውም በጎንደር ከተማ የተከናወኑ የልማት ሥራዎች የከተማዋን ታሪካዊነት የሚመጥን እና ውብ ገጽታን ያላበሰ መኾኑን ተናግረዋል።

ከተማዋ የቱሪስት መዳረሻ በመኾኗ ለጎብኝዎች ምቹ እንድትኾን የሚያስችል ስለመኾኑም አስተያየታቸውን ሰጥተዋል። በቀጣይ ሥራቸውም ጎንደር ከተማን ለማስተዋወቅ የሚያግዝ ጉብኝት ማድረጋቸውን ነው የተናገሩት።

የአማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን ጎንደር ቅርንጫፍ ዋና አዘጋጅ እመቤት ሁነኛው በጎንደር ከተማ እየተከናወኑ ያሉ የልማት ሥራዎች ምልከታ ለቀጣይ የዘገባ ሥራዎች ውጤታማነት የሚያግዝ መኾኑን ገልጸዋል። የኮሪደር ልማት ሥራውም ከተማዋን ምቹ እና ውብ እንዳደረጋት ተናግረዋል።

ዘጋቢ: ቃልኪዳን ኃይሌ

የአሚኮየአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን

Previous articleከ94 ሺህ በላይ የኅብረተሰብ ክፍሎችን ተጠቃሚ የሚያደርግ የንጹሕ መጠጥ ውኃ ጋን አገልግሎት ጀመረ።
Next articleየቆቦ ጊራና መስኖ ልማት ኘሮጀክትን ወደ ሥራ ለማስገባት እየተሠራ ነው።