
ወልድያ: የካቲት 11/2017 ዓ.ም (አሚኮ) የክልል እና የዞን ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኀላፊዎች በሰሜን ወሎ ዞን ቆቦ ከተማ አሥተዳደር የተሠራ የንጹሕ መጠጥ ውኃ ማጠራቀሚያ ጋን መርቀው ሥራ አስጀምረዋል። ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኀላፊዎቹ በሰሜን ወሎ ዞን ቆቦ ከተማ የተሠሩ የልማት ሥራዎችንም እየጎበኙ ነው።
ለአገልግሎት ክፍት የኾነው የውኃ ማጠራቀሚያ ጋኑ አንድ ሚሊዮን ሊትር ውኃ የማያዝ አቅም እንዳለው ተመላክቷል። ሥራው 10 ነጥብ 5 ሚሊዮን ብር ወጭ የተደረገበት መኾኑም ተገልጿል። ከ94 ሺህ በላይ የኅብረተሰብ ክፍሎችን ተጠቃሚ ያደርጋል ነው የተባለው። ጋኑ የቆቦ ከተማን ሕዝብ የንጹህ መጠጥ ውኃ እጥረት እንደሚቀርፍ ተመላክቷል።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!