ትርፍ እና ታሪፍን ለመቆጣጠር ኢ-“ቲኬቲንግ እየተጠቀመ መኾኑን የአማራ ክልል ትራንስፖርት እና ሎጂስቲክስ ባለሥልጣን አስታወቀ።

27

ባሕር ዳር: የካቲት 11/2017 ዓ.ም (አሚኮ) የኢንፎርሜሽን፣ የኮሙኒኬሽን እና የቴክኖሎጂ አሠራርን ውጤታማነት ማሻሻል በባለስልጣኑ ትኩረት ከተሠጣቸው ተግባራት አንዱ ነው። የትራንስፖርት ዘርፉን ለማዘመን የመረጃ ማዕከል በማቋቋም የአሽከርካሪ እና ተሽከርካሪ መረጃዎችን በሲስተም የማደራጀት ሥራ መሠራቱን የአማራ ክልል ትራንስፖርት እና ሎጅስቲክስ ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ዘውዱ ማለደ ገልጸዋል።

የትራፊክ ኮምፕሌክስ ግንባታ እና የማዘመን ሥራ ተሠርቷል ብለዋል። ከዚህ ውስጥ ደግሞ አንዱ በ190 ሚሊዮን ብር በእንጅባራ ከተማ እየተገነባ የሚገኘው የትራፊክ ኮምፕሌክስ ነው። የግንባታ ሂደቱ 33 በመቶ ላይ መድረሱን ገልጸዋል። ሌሎች አምስት ነባር ትራፊክ ኮምፕሌክሶችን ደግሞ 222 ሚሊዮን ብር በመመደብ የማሻሻል እና የማዘመን ሥራ እየተሠራ መኾኑን አንስተዋል።

ሌላው በበጀት ዓመቱ ከተከናወኑ የትራንስፖርት መሠረተ ልማት ሥራዎች ውስጥ የሕዝብ ትራንስፖርት መናኽሪያዎች ግንባታ እና ማዘመን ሥራ ነው። በስድስት ወሩ 18 ሚሊዮን ብር በመመደብ በደብረ ማርቆስ ከተማ መናኽሪያ ግንባታ እየተከናወነ ይገኛል። አጠቃላይ የመናኽሪያ ግንባታው እስከ 362 ሚሊዮን ብር ይጨርሳል ተብሎ ይጠበቃል። ከዚህም ባለፈ ከማኅበረሰቡ ተሳትፎ፣ ከመዘጋጃ ቤቶች እና መንግሥታዊ ካልኾኑ ድርጅቶች በተገኘ 38 ሚሊዮን ብር 31 ነባር መነኻሪያዎችን የመጠገን እና በቴክኖሎጂ የማዘመን ሥራ እየተሠራ መኾኑን ገልጸዋል።

ታሪፍ እና ትርፍን ለመቆጣጠር በሰባት የዞን እና በ166 ከተሞች በሚገኙ መናኽሪያዎች የኢ-ቲኬቲንግ አሠራርን የማስፋት ሥራ መሠራቱን ገልጸዋል። ያልጀመሩ መናኽሪያዎችም በቀጣይ እንዲጀምሩ ትኩረት መሰጠቱንም ነው ዋና ዳይሬክተሩ የገለጹት።

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleየወተት ሃብት ልማት በጎንደር ከተማ
Next articleከ94 ሺህ በላይ የኅብረተሰብ ክፍሎችን ተጠቃሚ የሚያደርግ የንጹሕ መጠጥ ውኃ ጋን አገልግሎት ጀመረ።