“የኢትዮጵያ የማንሠራራት ጉዞ የሚሳካው በተቋሞቻችን ጥንካሬ ነው” ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመሥገን ጥሩነህ

19

ባሕር ዳር፡ የካቲት 11/2017 ዓ.ም (አሚኮ) ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመሥገን ጥሩነህ በማኅበራዊ ገጻቸው ባሥተላለፉት መልእክት ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ተጠሪ የሆኑ አስፈጻሚ አካላትን የ2017 በጀት ዓመት የግማሽ ዓመት አፈጻጸም፣ ዛሬ ገምግመናል ብለዋል፡፡

ባለፉት ስድስት ዓመታት መንግሥታችን ለጠንካራ ተቋማት ግንባታ በልዩ ትኩረት ሠርቷል። በተለይም ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ተጠሪ የሆኑ ተቋማት ራሳቸውን በአግባቡ በማደራጀት ለሀገር ግንባታ የሚቆጠር አስተዋፅዖ በማበርከት ላይ መሆናቸውን ገልጸዋል።

በፖለቲካ፣ በኢኮኖሚና በማህበራዊ መስኮች ባለፉት ስድስት ወራት የተመዘገቡ ስኬቶች የተቋሞቻችን የመፈጸም አቅም ማሳያ ናቸው ብለዋል።

በቀጣይም ተቋማቱ የኢትዮጵያን የከፍታ ጉዞ ለማሳካት አገልግሎት አሰጣጣችንን ማዘመን፣ ወጪ ቆጣቢ አሰራርን መከተል፣ ቅንጅታዊ አሰራርን ማጠናከር እና በተሰጠን ተልዕኮ የምንፈጥረውን በጎ ተፅዕኖ እንዲሁም የተገኙ ውጤቶችን በቀጣይነት እየገመገሙ መሄድ አስፈላጊ መሆኑን አቅጣጫ አስቀምጠናል ብለዋል፡፡

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!

https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleየተቀላጠፈ አገልግሎት ለተገልጋዮች መስጠት የሚያስችል ሶፍትዌር ወደ ሥራ ሊገባ ነው።
Next article144 የአሽከርካሪ ማሠልጠኛ ተቋማት በቴክኖሎ የታገዘ ሥልጠና እንዲሠጡ ተደርጓል።