192 ሚሊዮን ብር ወጭ የተደረገበት የዱቄት ፍብሪካ ተመረቀ።

59

ወልዲያ: የካቲት 11/2017 ዓ.ም (አሚኮ) የክልል እና የዞን ከፍተኛ የሥራ ኀላፊዎች በሰሜን ወሎ ዞን ራያ ቆቦ ወረዳ የተገነባ የዱቄት ፋብሪካን መርቀዋል። የሥራ ኀላፊዎቹ በራያ ቆቦ ወረዳ አራዱም 08 ቀበሌ ሲገነባ የቆየን ጎሊና የዱቄት ፋብሪካን ነው የመረቁት።

ፋብሪካው 192 ሚሊዮን ብር ወጭ የተደረገበት ሲኾን በአራት ወራት ተሠርቶ እንደተጠናቀቀ ተገልጿል። በቀን 400 ኩንታል የማምረት አቅም አለውም ተብሏል። የአማራ ክልል ምክትል ፕሬዝዳንት አብዱ ሁሴን (ዶ.ር) ዱቄት ፋብሪካው በአጭር ጊዜ ተገንብቶ መጠናቀቁ በአካባቢው የተረጋጋ ሰላም መኖሩን ማሳያ ነው ብለዋል።

የክልሉ አምራች ኢንዱስትሪዎች የማምረት አቅማቸው 60 በመቶ እንዲጨምር ለማድረግ የክልሉ መንግሥት ጋር በመነጋገር የኤሌክትሪክ ኃይል እና ሌሎች መሠረተ ልማቶች እንዲሟሉ ያደርጋል ብለዋል። የሰሜን ወሎ ዞን ዋና አሥተዳዳሪ አራጌ ይመር አካባቢው ለዱቄት ፋብሪካው የሚኾን ግብዓት ለማግኘት አመች እንደኾነ ተናግረዋል። የቆላ መስኖ ስንዴ ማምረት የሚያስችል ጸጋ ያለበት እንደኾነም ገልጸዋል።

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleየምክክር ኮሚሽኑ የሥራ ዘመን ተራዘመ።
Next articleየተቀላጠፈ አገልግሎት ለተገልጋዮች መስጠት የሚያስችል ሶፍትዌር ወደ ሥራ ሊገባ ነው።