የምክክር ኮሚሽኑ የሥራ ዘመን ተራዘመ።

20

ባሕር ዳር: የካቲት 10/2017 ዓ.ም (አሚኮ) የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በ4ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 1ኛ አስቸኳይ ስብሰባው የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን የሦስት ዓመታት የሥራ አፈፃፀም ሪፖርት በመመርመር ለኮሚሽኑ የ1 ዓመት ተጨማሪ የሥራ ዘመንን ሰጥቷል።

በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የሕግ ጉዳዮች ኮሚቴ የኮሚሽኑን የሥራ ሂደት ከገመገመ በኋላ ባደረገው ምልከታ ኮሚሸኑ አጠቃላይ ሥራውን ማጠናቀቅ እንዲያስችለው የሥራ ዘመኑ ለአንድ ዓመት እንዲራዘም ምክረ ሃሳብ አቅርቦ ነበር፡፡

ምክር ቤቱ ኮሚሽኑ ዋና ዋና እና አንኳር ቀሪ ሥራዎች መኖራቸውን በማመን የሥራ ዘመኑ ለአንድ ዓመት እንዲራዘም በ3 ተቃውሞ በአብላጫ ድምፅ አፅድቋል።

አባላቱ ኮሚሽኑ በተሰጠው ተጨማሪ የሥራ ዘመን ተጠባቂ ቀሪ ሥራዎችን እንዲያጠናቅቅ ጠይቀዋል።

የኮሚሽኑ ማቋቋሚያ አዋጅ አስፈላጊ ኾኖ ሲገኝ የኮሚሽኑ የሥራ ዘመን በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ማራዘም እንደሚቻል ይደነግጋል።

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleባሕር ዳርን በማልማት ነዋሪዎቿን ተጠቃሚ ለማድረግ ከባለሃብቱ ጋር በትብብር እንደሚሠራ የባሕር ዳር ከተማ አሥተዳደር አስታወቀ።
Next article192 ሚሊዮን ብር ወጭ የተደረገበት የዱቄት ፍብሪካ ተመረቀ።