የአስቸኳይ ጊዜ አወጁን ለማስከበር የተጠናከረ ቁጥጥር እንደሚደረግ የባሕር ዳር ከተማ አስተዳደር አስታወቀ፡፡

146

ባሕር ዳር፡ ሚያዝያ 29/2012 ዓ.ም (አብመድ) በኢትዮጵያ በኮሮና ቫይረስ የሚያዙ ሰዎች ቁጥር ከዕለት ወደ ዕለት እየጨመረ ነው፡፡ ሚያዚያ 29/2012 ዓ.ም በፌደራል ጤና ጥበቃ ሚኒስቴር በኩል 25 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው መሰማቱ ደግሞ አስደንጋጭ እንደሚያደርገውና የበለጠ ጥንቃቄ ማድረግ እንደሚገባ የማንቂያ ደወል ነው፡፡

መዘናጋትን በማስቀረት በፊት የታየው ጥንቃቄ መቀጠል እንዳለበት የባሕር ዳር ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ አማረ ዓለሙ አሳስበዋል፡፡ በከተማው በአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ የተከለከሉ ጉዳዮችን በማክበር ራስንና ሌሎችንም ማዳን እንደሚገባም መልእክት አስተላለፈዋል፡፡

መጠጥች ቤቶ፣ ጫት ቤቶች እና መሰል አገልግሎት ሰጪ ተቋማት ላይ ወደ ቀድሞ የተለመደው ሥራቸው የመመለስ ተግባር እየታየባቸው መሆኑን አቶ አማረ ጠቁመዋል፡፡ በተቋማቱ ላይ ከነገ ሚያዚያ 30/ 2012 ዓ.ም ጀምሮ የተጠናከረ ቁጥጥርና ክትትል እንደሚደረግም ምክትል ከንቲባው ተናግረዋል፡፡

የባሕር ዳር ከተማ ነዋሪዎችም ለ14 ቀናት ከቤት ያለመውጣት ትዕዛዙን ተቀብለው እንደፈፀሙ ሁሉ አሁንም ጥንቃቄውን አጠናክረው እንዲገፉበት ጥሪ አቅርበል፡፡ በዚህም የግል፣ የቤተሰብና እንደ ሀገር የሚጠፋውን ሕይወት መታደግ እንደሚገባ ምክትል ከንቲባው መልእክት አስተላልፈዋል፡፡

ዘጋቢ፡- ኪሩቤል ተሾመ

Previous articleየውጭ ሀገር ጉዞ ታሪክና ከታማሚ ጋር ንክኪ የሌላቸው 19 ሰዎችን ጨምሮ በ25 ሰዎች ላይ የኮሮና ቫይረስ ተገኘ፡፡
Next articleየክልሉ መንግሥት የተፈጠረውን ችግር መርምሮ የታክስ ምሕረት ማድረጉ ለቀጣይ ሥራቸው ተስፋ እንደሚሰጥ አስተያዬታቸውን የሰጡ ባለሀብቶች ገለጹ፡፡