
ባሕር ዳር: የካቲት 11/2017 ዓ.ም (አሚኮ) የባሕር ዳር ከተማ አሥተዳደር ኢንዱስትሪ እና ኢንቨስትመንት መምሪያ ”ኢትዮጵያ ታምርት፤ እኛም እንሸምት” በሚል መሪ መልዕክት ከከተማ አሥተዳደሩ ባለሀብቶች እና አጋር አካላት ጋር ውይይት እያካሄደ ነው።
የአማራ ክልል ኢንዱስትሪ እና ኢንቨስትመንት ቢሮ ኀላፊ እንድሪስ አብዱን ጨምሮ የክልል እና የከተማ አሥተዳደሩ መሪዎች ተገኝተዋል።
የምርት አውደ ርዕዩን የአማራ ክልል ኢንዱስትሪ እና ኢንቨስትመንት ቢሮ ኀላፊ እንድሪስ አብዱ እና የባሕር ዳር ከተማ አሥተዳደር ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ ጎሹ እንዳላማው አስጀምረውታል።
አምራቾችም ምርቶቻቸውን ለእይታ እና ለሽያጭ አቅርበዋል።
ውይይቱ የከተማዋን ኢንቨስትመንት የማነቃቃት ዓላማ ያለው ሲኾን የክልል እና የከተማ አሥተዳደሩ ከፍተኛ መሪዎች ተገኝተዋል።
ዘጋቢ፦ ዋሴ ባየ
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!