
ወልድያ: የካቲት 10/2017 ዓ.ም (አሚኮ) የአማራ ክልል እና የሰሜን ወሎ ዞን ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኀላፊዎች በሰሜን ወሎ ዞን የጋሸና ከተማ አሥተዳደር ሁለገብ የቢሮ አገልግሎት መስጫ ሕንጻ ግንባታን አስጀምረዋል። የአማራ ክልል ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ፋንቱ ተስፋዬ፣ የአማራ ክልል ምክትል ርእሰ መሥተዳደር አብዱ ሁሴን (ዶ.ር)፣ የሰሜን ወሎ ዞን ዋና አሥተዳዳሪ አራጌ ይመር እና ሌሎች ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኀላፊዎች ሥራውን አስጀምረዋል።
ሕንጻው ባለስምንት ወለል ሲኾን በከተማ አሥተዳደሩ ሙሉ ወጭ የሚገነባ መኾኑን የጋሸና ከተማ አሥተዳደር ከንቲባ ፀጋ ውቤ ገልጸዋል።
የአማራ ክልል ምክትል ርእሰ መሥተዳደር አብዱ ሁሴን (ዶ.ር) ይህ የመሠረተ ልማት የሥራ ማስጀመሪያ ውጤት ላይ ሲደርስ ድርብ ደስታ ይኾናል ብለዋል።
ሥራው ተጠናቅቆ ለምረቃ ሲበቃ ውጤታማ መኾኑ እንደሚረጋገጥ ገልጸው ለዚህም በትጋት ልትሠሩ ይገባል ሲሉ አሳስበዋል።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!